Abdu Kiar Wey Gude Скачать

Abdu Kiar Wey Gude

Abdu Kiar

Wey Gude

15 прослушиваний
05:30
Все треки Abdu Kiar Текст песни
Слушать
Скачать песню

Текст песни «Wey Gude»

Abdu Kiar

ፍቅርሽ አንድ አንድ እያለ
ልቤ ውስጥ ተደላደለ
ተደላድሎስ መቼ ቀረ?
ያስተክዘኝ ጀመረ
ስትጠፊ የሚያስጨንቀኝ
በሀሣብ የሚያንፏቅቀኝ
ልንገርሽ ውዴ መውደዴ
ፍቅርሽ ነው ሰሞኑን ጉዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
አቤት የኔ ነገር ይገርማል ለጤና ያርግልኝ ጌታዬ
ምነው ቢቀርብኝ እላለሁ ሲበዛ ጭንቀቴ ስቃዬ
ደሞ ደስታሽን ሳየው በዓይኔ ሀሳቤን እረሳና ድካሜን
ጭራሽ ጣፍጦኝ ቀረ ስቃዬ ወደድኩት ወደድኩት ህመሜን
ሰው ህመሙን ወዶ፤ ሰው ስቃዩን ወዶ
እንዴት ነው የሚኖረው እንዴት ነው የሚዘልቀው ሰው ገዳዩን ወዶ
ፍቅር እንዲህ አይደል ወይ ታምኖ መገኘት
የወደዱትን ሰው ያፈቀሩትን ሰው ሲደሰት ማየት
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ፍቅርሽ አንድ አንድ እያለ
ልቤ ውስጥ ተደላደለ
ተደላድሎስ መቼ ቀረ?
ያስተክዘኝ ጀመረ
ስትጠፊ የሚያስጨንቀኝ
በሀሣብ የሚያንፏቅቀኝ
ልንገርሽ ውዴ መውደዴ
ፍቅርሽ ነው ሰሞኑን ጉዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
እንዳልቀየምሽ አርጎኛል- ቂም እንዳልይዝብሽ አርጎኛል
ልቤ ፍቅርን አምኖ ሁልጊዜ ልክ ናት ልክ ናት ይለኛል
ምታመመው በፍቅርሽ ሆኗል ምድነውም በፍቅርሽ ሆኗል
አዕምሮዬም ብዙ እያለመ ሰሞኑን እንደማይሆን ሆኗል
ህልምን እኔ ሣውቀው ሌሊት በማታ ነው
ወይ... ጉዴ ሰሞኑን ከእንቅልፌ የምነቃው አንቺን ለማለም ነው
እንደዚህ የምሆነው ለምን ይመስልሻል
ስለወደድኩሽ ነው ስላፈቀርኩሽ ነው መቼ ይጠፋሻል
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ
ወይ ጉዴ
አንቺን መውደዴ

На странице доступен трек Wey Gude от Abdu Kiar (05:30). Слушайте онлайн или загрузите в mp3 в один клик бесплатно на свое устройство — выше есть текст песни.

Другие песни Abdu Kiar

Свежее на Muzfrog

Все новинки →