Michael Belayneh Lekas Lebego New Скачать

Michael Belayneh Lekas Lebego New

Michael Belayneh

Lekas Lebego New

Слушать
Скачать песню

Текст песни «Lekas Lebego New»

Michael Belayneh

በይቅር ታሽቶ ታክሞ በካሳ
የማይድን ህመም የማይሽር ጠባሳ
ልቤ ላይ ትታው መራቋ ከጎኔ
ለመርሳተ ፍቅሯን ሆነልኝ ሰበቤ
እሷን ልጣ እሷን እንደ መውደዴ
በውበት ቅርጿ እንደመማረኬ
ባይሆን የራቀች አስቀይማ ሆዴን
ይታየኝ ነበር የማጣት ማበዴን
ባልታሰበ ማዕበል ድንገት መመታቴ
ለካስ ለበጎ ነው ይህ ሁሉ ማየቴ

አይኔ አሁንማ ይቅር ሊናፍቃት
ትዝ ብላው ድንገት ቢሞክር በሀሳብ ሊስላት
ቀድሞ እየታየው ከመልኳ ስራዋ በደሏ
ሊስላት አቃተው ጠፍቶበት ውበቷ ምስሏ
ያን በደሏን እስኪ በአፌ ልመርቀው
ኑርልኝ እድሜ ይስጥህ ያክርምህ በልቤ ልበለው
ሆኖልኛል እና ምክንያትም ሰበብ ሰበቤ
ፍቅር ትዝታዋን ለማውጣት ከሀሳብ ከልቤ

በይቅር ታሽቶ ታክሞ በካሳ
የማይድን ህመም የማይሽር ጠባሳ
ልቤ ላይ ትታው መራቋ ከጎኔ
ለመርሳተ ፍቅሯን ሆነልኝ ሰበቤ
ሀጥያቷ ቀስ በቀስ ቢሆንስ ምን ነበር
አይቼው ቢበዛ ቢፈፀም እያደር
ከራሴ በልጣ እሷን እንደ መውደዴ
በውበት ቅርጿ እንደመማረኬ
ባይሆን የራቀች አስቀይማ ሆዴ
ይታየኝ ነበር የማጣት ማበዴ
ለካስ ልብ እንደ ሰው አይቶ የሚርደው
የሚወስንበት አጥቶ ቢቃትት ነው

ያን በደሏን እስኪ በአፌ ልመርቀው
ኑርልኝ እድሜ ይስጥህ ያክርምህ በልቤ ልበለው
ሆኖልኛል እና ምክንያትም ሰበብ ሰበቤ
ፍቅር ትዝታዋን ለማውጣት ከሀሳብ ከልቤ

አይኔ አሁንማ ይቅር ሊናፍቃት
ትዝ ብላው ድንገት ቢሞክር በሀሳብ ሊስላት
ቀድሞ እየታየው ከመልኳ ስራዋ በደሏ
ሊስላት አቃተው ጠፍቶበት ውበቷ ምስሏ

На странице доступен трек Lekas Lebego New от Michael Belayneh (06:21). Слушайте онлайн или загрузите в mp3 в один клик бесплатно на свое устройство — выше есть текст песни.

Свежее на Muzfrog

Все новинки →